ስለ ኮርፖሬሽኑ
የኮርፖሬሽኑ ታሪክ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከተማው ነዋሪ የሚሰጠውን አገልግሎት ግልጽ፣ ፈጣንና ውጤታማ እንዲሆንና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በርካታ የለውጥ ስራ ተግባራዊ እያደረገ ሲሆን ከዚህም መካከል የከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት እንደገና በማቋቋም መዋቅራዊ አደረጃጀትና የመሰረታዊ የስራ ሂደት ክለሳ ጥናት በማካሄድ ተቋማት እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡
በዚሁ መሰረት ቀደም ሲል የነበሩት ሶስት ተቋማት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት (20/80) – በከተማው አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 15/1996 የተቋቋመና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የከተማው ነወሪዎች ቤት ለማቅረብ ያለመ፤ የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ (40/60) – በከተማው አስተዳደር ደንብ ቁጥር 45/2004 የተቋቋመና መካከለኛ ገቢ ላላቸው የከተማው ነዋሪዎች ቤት ለማቅረብ ያለመ እንዲሁም የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲን – ግንባታቸው የተጠናቀቁ ቤቶችን ከ20/80 እና ከ40/60 በመረከብ ፍትሀዊ በሆነ ለነዋሪዎች ለማስተላለፍና ለማስተዳደር የተቋቋመውን በማዋሃድ የከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት እንደገና በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀፅ 66 መሰረት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡
በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ በማዕከልና ፕ/ቅ/ጽ/ቤቶች የተደራጀ ሲሆን በማዕከል ደረጃ በአምስት ዘርፎች፣ በ21 ዳይሬክቶሬቶች እና በ37 ቡድኖች እንዲሁም በፕ/ቅ/ጽ/ቤት ደረጃ በሁለት ዘርፎች፣ በሦስት ዳይሬክቶሬቶችና በስምንት ቡድኖች ተደራጅቷል፡፡
1. በቢሮ የሚቀርበውን መረጃ መሠረት በማድረግ የሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የስትራቴጂያዊና ዓመታዊ የፉሲካልና የፊይናንሻል ዕቅድ ያዘጋጃል፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ያዳብራል፤ በሚመለከተው አካል አጸድቆ ተግባራዊ ያደርጋል፤
2. ለጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ የሚያስፈልገውን የለማ መሬት ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ያቀርባል፤ ሲፈቀድ ይረከባል፤
3. ለቤቶች ግንባታ የሚያስፈልገውን ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላን እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
4. የሚገነቡ ቤቶችን የታይፖሎጂ ዲዛይንና ዝርዝር ዲዛይን እንዱሁም ስፔስፊኬሽን እና የስራ ዝርዝር ይሰራል ወይም እንዲሰራ ያደርጋል፤ የተዘጋጁ ዲዛይኖችን ከግንባታ ሳይቶች ጋር የማጣጣም ስራ ይሰራል ወይም እንዲሰራ ያደርጋል፤
5. የፕላን ስምምነትና የግንባታ ፈቃድ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ በማቅረብ ያስፈጽማል፤ ይረከባል፤
6. ለቤቶቹ ልማት የሚያስፈልገውን ገንዘብ በከተማ አስተዳደሩ ዋስትና ከአበዲሪው ባንክ ይበደራል፤ በቤት ልማት ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ለመሆን የተመዘገቡና በባንክ የሚቆጥቡ የነዋሪዎችን ቁጠባ ለመጠቀም የብድር ወለድ ምጣኔውን በተመለከተ ከባንኩ ጋር ድርድር ያደርጋል፤
7. ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከባንክ የተገኘው ብድር፣ ቤቶቹ ሲተላለፉ የተገኘው ገቢ፣ የተመለሰው የብድር መጠን እና ወለድ በአግባቡ ይመዘግባል ወቅታዊ የሂሳብ ሪፖርት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
8. ግንባታውን የሚያከናውኑ አማካሪዎችንና ስራ ተቋራጮችን አግባብ ባለው ህግ ይመዘግባል፤ ይመለምላል፤ ወደ ስራ ያሰማራል፤
9. የቤቶች ልማትን ማካሄድ የሚያስችል ውሎችን ያዘጋጃል፤ ይዋዋላል፤ ውሉንም ያስተዳድራል፤
10. ለግንባታና ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ የሚያስፈልገውን መሠረተ-ልማት እንዲሟላ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ያቀርባል፤ መሟላቱንም ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፤
11. የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በተገባው ውል መሠረት፣ የጥራት ደረጃ፣ የጊዜና የዋጋ ገደብ ተጠብቆ መሠራቱን ለማረጋገጥ የሚያስችል የቁጥጥር ስርዓት ይዘረጋል፤ በበላይነትም ይቆጣጠራል፤ ግንባታቸው ሲጠናቀቅ ርክክብም ይፈጽማል፤
12. የህንጻው ግንባታ ሲጠናቀቅ ለመሰረተ ልማት ቅንጅት፣ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዱሁም ለሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት የመጠቀሚያ ፈቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ ያቀርባል፤ ክትትል በማድረግም ፈቃዱን ይረከባል፤
13. ግንባታቸው የተጠናቀቁና የመጠቀሚያ ፈቃድ ያገኙ የመኖሪያ ቤቶችን የማስተላለፊያ ዋጋ በማጥናት እንዲጸዴቅ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
14. ግንባታቸው ተጠናቆ የመጠቀሚያ ፈቃድ ያገኙ የመኖሪያ ቤቶችን በማስተላለፊያ ዋጋቸው ለተጠቃሚዎች በዕጣ ወይም በምደባ ያስተላልፋል፤ የቤቶቹን አስፈሊጊ ሰነዶች በሙሉ ቤቱ ለደረሳቸው ባለመብቶች በወቅቱ ያስረክባል፤
15. በሚገነቡ የጋራ ህንጻዎች ለንግድ አገልግሎት የሚውሉትን ቤቶች በጨረታ ይሸጣል፤
16. ለኪራይ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን ያስገነባል፤ ያከራያል፣ ያስተዳድራል፤
17. የሚያስገነባቸው ቤቶች ወጪ ቆጣቢና ጥራታቸው የተጠበቁ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፤
18. ከአበዳሪው ባንክ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ወቅታዊና መሠረታዊ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል ስርዓት ይዘርጋል፤ ተግባራዊም ያደርጋል፤
19. በውሉ መሰረት ባልተፈጸሙ፣ በሚታዩ ጉድለቶችንና ጥፋቶች ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡
20. በጋራ መኖሪያ ቤቶች ህብረተሰቡን የሚያውኩ እና ህገወጥ ተግባራትን የሚፈፅሙ አካሊትን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ቁጥጥር ያደርጋል፤ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
21. ኢ-መደበኛ የሆኑ የመኖሪያ ቤት አቅርቦቶች መረጃ ይሰበስባል፤ በመደበኛው የቤቶች ልማት ፕሮግራም ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ በማጥናት ወደ መደበኛው ፕሮግራም የሚገቡበት የመፍትሔ ሀሳብ ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፤ የመፍትሔ ሀሳቡ ተቀባይነት ሲያገኝ ተግባራዊ ያደርጋል፤
22. ቤቶቹ በልማት ምክንያት በሚፈርሱበት ወቅት አስፈሊጊውን መረጃ ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፤ በቤቱ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ምትክ ቤት የሚያገኙበትን አግባብ ያመቻቻል፤
23. የመንግስት የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በህገ-ወጥ መንገድ ከያዙት አካላት ያስለቅቃል፤
24. የሚያስተዳድራቸውን ቤቶች መረጃ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይይዛል፤ ለቤቶቹ ጥገናና እድሳት ያደርጋል፡፡
25. የሚያስተድዳራቸውን፣ ያስተላለፋቸውን፣ የሚያስተላልፋቸውን እና እየተገነቡ ያሉ ቤቶችን በመረጃ ቋት የማደራጀት እና የማስተዳደር፣ እንደአስፈላጊነቱ መረጃውን ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ካሉ ከኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጋር የማስተባበር ሥራ ያከናውናል፤