እንኳን ወደ የኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!

ዳይሬክቶሬቱ ሁለት ቡድኖች አሉት

  1. የጨረታ ቡድን
  2. የኮንትራት አስተዳደር ቡድን
  3. የዋጋ ጥናትና ትንተና ቡድን

    በዳይሬክቶሬቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች፤

    • የሥራ ተቋራጮች፣ የአማካሪዎች መምረጫ መስፈርት በማዘጋጀት ለጨረታ እንዲከናወን ማድረግ፤
    • የውል/ኮንትራት ሥራዎች ማስረዳደር፤
    • የግንባታ እና ተያያዥ ዋጋዎችን ማስጠናት፣ መተንተን፣ ማስወሰን፣ማፅደቅ ተግራራዊ እንዲሆን ማድረግ፤

    በሶስቱ ቡድኖች የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች

    1. የሥራ ተቋራጮችና የአማካሪ ድጅቶች መምረጫ ዝክረ ተግባር /TOR/ ማዘጋጀት፣ ማፅደቅ፣መተግበር፤

    2. በግዢ መምሪያ መሠረት የመምረጫ መስፈርት ይዘጋጃል እንዲፀድቅ ይደረጋል፡፡

    3. የግዢ ሂደቱን የጠበቀ የጨረታ ሠነድ ይዘጋጃል እንዲፀድቅ ይደረጋል፡፡

    4. የውል ረቂቅ ማዘጋጀትና ማፅደቅ፤

    5. የተዘጋጀውንና የፀደቀውን የውል ሰነድ ማዳበርና ማዋዋል፡፡

    6. የኮንትራት/ውል አስተዳደር ተግባራት ማስተባበርና መከታተል፡፡

    7. የውል ሰነዱን ለሚመለከታቸው እንዲደርስ ማድረግ፣ ማስፈፀም፡፡

    8. የግንባታ በጀት አፈፃፀም እና የግንባታ አፈፃፀም ደረጃን መከታተል፡፡

    9. የውል ለውጥ /የሚያስከትሉ/ የሚያጋጥሙ ካሉ በማጥናትና በማጣራት የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ፣ በማፀደቅና አተገባበሩን መከታተል፡፡

    10. በኮንትራት አስተዳደር ዙሪያ ከባለቤት፣ ሥራ ተቋራጭ፣ አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ ጋር ለሚቀርቡ የይገባኛል /Claims/ በመከታተል በውሉ መሠረት መፍትሔ እንዲያገኝ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፡፡

    11. የቅድመ-ክፍያ ዋስትና እና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና በውሉ መሠረት ወቅታቸውን ጠብቀው ተግባራዊ መደረጋቸውን መከታተል፡፡

    12. የግንባታ ሥራ፣ የጉልበት ዋጋ ጥናትና ትንተና በማከናወን በማረጋገጥ ማስወሰን፣ ማፅደቅና ተግባራዊ እንዲደረግ መከታተል፡፡

    13. የቤት ማስተላለፊያ ዋጋ የግንባታው ሂደት ክትትል ማድረግ ማጥናት፣ መተንተን እና በማረጋገጥ እንዲፀድቅ ሆኖ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፡፡

    14. በውሉ መሠረት የተዘጋጀ የቅድመ ግንባታ የፀደቀ ዋጋ ተገቢነቱን ማረጋገጥ፡፡