የግዥ ጨረታ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

የውሃ ፓምፕ/Water Pump/ አቅርቦት፣ ገጠማ፣ ቴስቲንግ እና ኮሚሽኒንግ (Supply, installation, testing, and commissioning) ግዥ

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/013/2016   

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የውሃ ፓምፕ/Water Pump/ አቅርቦት፣ ገጠማ፣ ቴስቲንግ እና ኮሚሽኒንግ (Supply, installation, testing, and commissioning) ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዘርፉ የ2016 የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ ንግድ ምዝገባ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድህረ ገፅ /Online/ የተመዘገቡ እንዲሁም ማስረጃቸውን ኮፒና ኦርጅናል አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ያለው አዲስ ህንፃ ላይ 4ተኛ ፎቅ በኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ 9ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 901 ይከፈታል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የካቲት 16/2016 የወጣውን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ማየት ይቻላል፡፡

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01  

    ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማት ህንፃ

             ስልክ ቁጥር 0115 58 37 11/ 0115 58 34 70

በቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን