እንኳን ወደ የግንባታና መሠረተ ልማት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!

ዳይሬክቶሬቱ ሁለት ቡድኖች አሉት

  1. የመሰረተ ልማት ክትትል ቡድን
  2. የግንባታና ግብዓት ክትትል ቡድን

    በዳይሬክቶሬቱና በሁለቱ ቡድኖች የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች

    የግንባታ ክትትል ቡድን፡

    1. በህንጻ ግንባታ ላይ የሚደረጉ የክትትል እና ቁጥጥር ሥራዎች በአግባቡ አንዱከናወኑ ማድረግና ማረጋገጥ፤

    2. የግንባታ፣ የግንባታ ግብአት ጥራት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣

    3. ክፍያዎችን በስታንዲርድና በውል መሰረት ማጣራት እና ማረጋገጥ

    4. የህንጻዎች ግንባታ በዲዛይን መሰረት መሰራታቸውን በማረጋገጥ ደረጃቸውን የጠበቁ የህንጻ ግንባታዎች ተፈፃሚነት መከታተል እና ማረጋገጥ ነው፤

    የመሰረተ ልማት ክትትል ቡድን፡

    1. ለግንባታ ስራ የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ ለማድረግ ለአቅራቢ ተቋማት ክፍያዎችን በመፈጸም መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ ማድረግ፤

    2. የተለያዩ ለመሰረተ ልማት ስራዎች የሚደረጉ የክትትል ሥራዎች በአግባቡ እንዲከናወኑ ማድረግ እና የተቀናጀ ዕቅድ አውጥቶ በጋራ መስራት

    3. የመሰረተ ልማት ስራዎች ጥራታቸውን የጠበቁ፤ በተቀመጠው ጊዜ፣በተቀመጠው ወጪ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እንዲከናወኑ ማድረግ፤

    4. ክፍያዎችን በስታንዳርድና በውል መሰረት ማጣራት እና ማረጋገጥ፤

    5. የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በዲዛይን መሰረት መሰራታቸውን በማረጋገጥ በኮርፖሬሽኑ ስር ደረጃቸውን የጠበቁ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ተፈፃሚነት መከታተል እና ማረጋገጥ፤

    6. ለነዋሪው የሚያገለግሉ መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ ለመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ክፍያዎችን መፈጸም እና መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ ማድረግ፤

    7. በሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚገነቡ የመሰረተ ልማት ስራዎችን መከታተልና መቆጣጠር፤