እንኳን ወደ የኦዲት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!

ዳይሬክቶሬቱ ሁለት ቡድኖች አሉት

  1. የክዋኔ ኦዲት ቡድን
  2. የፋይናንስ ኦዲት ቡድን

    መግቢያ

    የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ጽንሰ ሐሳብ የባለበጀት መ/ቤቶች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሀብትና ንብረት ደንብና መመሪያ ተከትለው እየሰሩ መሆኑንና ከማዕከል እስከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ድረስ የኦዲት ስራ በቅደም ተከተልና የስራ ፕሮግራም የፋይናንሻል፣ ክዋኔ ኦዲት እና ሌሎችንም ኦዲቶች በማከናወን ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ ነው፡፡

    በዳይሬክቶሬቱና በሁለቱ ቡድኖች የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች

    1. ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመለትን ዓላማ ከሕጎች፣ ከአዋጆች፣ ከደንቦችና ከመመሪያዎች አንጻር ማሳካቱን ማረጋገጥ፤

    2. የምክር አገልግሎትን መስጠትና ለኮርፖሬሽኑ የስራ እንቅስቃሴ ተጨማሪ እሴት መፍጠር፤

    3. በኮርፖሬሽኑ ያሉትን የስራ ዘርፎቸች አስተዳደር የውስጥ ቁጥጥርና የስራ አመራር ሂደት የአሰራር ሥርዓት በመፈተሸ ስጋት ያለባቸውን በመለየት ሥራቱ እንዳይከሰት የሙያ ምክር አገልግሎት መስጠት፤

    4. የኮርፖሬሽኑን ዕቅዶችና  በጀት በሚገባ ለመምራትና ለማስተዳደርለተዘረጋው የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት እገዛ ማድረግ፤

    5. የመንግስት ገንዘብ ለታለመለትዓላማ በቁጠባ፣ በብቃትና ውጤታማ በሆነ ዕቅድ በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉንና የመንግስት ሃብትና ንብረት ከብክነት በሚገባ መጠበቁን ማረጋገጥና መከላከል፤

    6. በኮርፖሬሽኑ እየተዘጋጁ የሚቀርቡ ሪፖርቶች በዕለቱ የሚደረጉትን የስራ ክንውኖች ማካተታቸውንና ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ፤

    7. በመንግስት ሀብት ላይ ብክነት ሲደርስ የጉድለቱን መጠንና ተጠያቂውን በመለየት ማሳካት እና ለወሰፊቱ እንዳይከሰት ለመከላከል እንዲቻል ለስራ አመራሩድጋፍ መስጠት

    8. ምክር የመስጠት ኃላፊነት

    9. የኦዲት ሪፖርት የመዛጋጀትና የመከታተል ኃላፊነት፤

    10. ማረጋገጫ የመስጠት ኃላፊነቶች፤

    11. ፋይናንሽያል ኦዲት ማድረግ፤

    12. የንብረት ገቢና ወጪ ኦዲት ማድረግ፤

    13. ክዋኔ ኦዲት ማድረግ፤

    14. ልዩ ኦዲት ማድረግ

    15. ኖርም ኦዲት ማድረግ  

    16. የክትትል ኦዲት ማድረግ

    17. የምክር አገልግሎት መስጠት፤