እንኳን ወደ የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!

ዳይሬክቶሬቱ ሁለት ቡድኖች አሉት

  1. የንብረት አስተዳደር ቡድን
  2. የጠቅላላ አገልግሎት ቡድን

    የንብረት አስተዳደር ስራዎች፡

    1. ንብረቶች ግዥ ተፈፅሞ ሲቀርብ በውለታ መሠረት መረከብ፤

    2. ከስቶር ወጪ የተደረጉ እቃዎች በቋሚ ንብረት መዝገብ ላይ መመዝገብ፤

    3. ንብረቶች በስርዓቱ መጋዘን ላይ መከማቸቱን ማረጋገጥ፤

    4. የቋሚ ንብረት ከስቶል ሲወጡ በግለሰቦች ስም መመዝገብ፤

    5. የቋሚ ንብረት የእርጅና ቅናሽ ማስላት፤

    6. የገቢና ወጪ ሰነዶችን ህትመት እንዲካሄድ በማድረግ ስራ ላይ እንዲውል ማድረግ፤

    7. የግንባታ ግብዓትስርጭትን እና ቁጥጥር መመራት፤

    8. የተሰራጨው የግንባታ ግብዓቶችን በአግባቡ እየመዘገቡ መሆኑን መቆጣጠር፤

    9. የጥበቃ ድርጅት ስራቸውን በአግባቡ እያከናወኑ መሆኑን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፤

    የጠቅላላ አገልግሎት ስራዎች፡-

    1. ወቅታዊ የተሸከርካሪዎችና ሰርቪስ የነዳጅና ቅባት ስርጭት በናሙና መሰረት መፈፀሙን መከታተልና ወርሃዊ ሪፖርት ማዘጋጀት፤

    2. የተሸከርካሪዎች ስምሪትና አጠቃቀም በመመሪያ መሠረት መሆኑ ስምሪቱና አጠቃቀሙን እየተገበረ መሆኑን ማረጋገጥ፤

    3. በማዕከልና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ያሉትን ተሸከርካሪዎች መረጃ ማሰባሰብ በማጠናከር ወቅታዊ ማድረግ፤

    4. የቢሮ ማስነሪዎችና ኮምፒውተሮች በወቅቱ ጥገና እንዲደረግላቸው የመከታተልና የማስተባበር ስራ መስራት፤

    5. የፎቶ ኮፒና ጥረዛ አገልግሎቶችን ማስተባበር፤