እንኳን ወደ የገበያ ትስስር ስልጠናና ክትትል ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!

ዳይሬክቶሬቱ ሁለት ቡድኖች አሉት

  1. የስልጠና እና ክትትል ቡድን
  2. የገበያ ትሥሥር ቡድን

    መግቢያ

    የገበያ ትስስር ስልጠናና ድጋፍ ክትትል  ዳይሬክቶሬት በኮርፖሬሽኑ የሚመደቡ ኢንተርፕራይዞችን የገበያ ትስስር በመፍጠር እና የስልጠና ድጋፍ በማድረግ በቅ/ጽ/ቤቶች ላይ የቤቶች ግንባታ ለኢንተርፕራይዞች ለማጠናከር የሚረዳ ዳይሬክቶሬት ነው፡፡ 

    በዳይሬክቶሬቱና በሁለቱ ቡድኖች የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች

    1. በኮርፖሬሽኑ ለኢንተርኘራይዞች የሚፈጠረውን የስራ ዕድል መምራትና መቆጣጠር፣

    2. የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የገበያ ትስስርና ሌሎች ሥራዎችን በተመለከተ የተሟላና ወቅታዊ መረጃ መያዛቸውን መከታተልና አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ፣

    3. በ18ቱም ቅ/ጽ/ቤቶች የስራ ዕድል የተፈጠረላቸውና በስራ ላይ ያሉ ኢንተርኘራይዞች መረጃ በየጊዜው ወቅታዊ /update/ በማድረግ ማደራጀት፣

    4. ለዳይሬክቶሬቱ የተሰጡትን ሥራዎች መከታተያ ቼክሊስት (Checklist) በማዘጋጀት የክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣

    5. በ18ቱም ቅ/ጽ/ቤቶች የስራ ዕድል የተፈጠረላቸውና በስራ ላይ ያሉ ኢንተርኘራይዞች የስልጠና ፍላጐት በመለየት ስልጠና መስጠት፣

    6. በተለየ የአመለካከትና የክህሎት ክፍተት በቅ/ጽ/ቤቶች በገበያ ትስስርና መረጃ ቡድን ውስጥ ላሉ ባለሙያዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠት፣