እንኳን ወደ የግንባታና ጥራትና ቤት ርክክብ ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!

ዳይሬክቶሬቱ ሁለት ቡድኖች አሉት

  1. የመሰረተ ልማት ክትትል ቡድን
  2. የግንባታ ግብዓት ክትትል ቡድን

    በዳይሬክቶሬቱና በሁለቱ ቡድኖች የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች

    1. በዲዛይን መስረት ቅድም ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውና ዝግጁ መሆናቸውን ወደ ግንባታው ስፍራ በመውረድ በማናበብ ማረጋገጥ፤

    2. በዲዛይኑ መሰረት እና በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ልክ ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ቋሚ የክትትል መረሃ ግብር በማዘጋጀት በግንባታው ስፍራ በመገኝት ማጣራት፤

    3. የተጠናቀቁ ቤቱችን በተገቢው ዲዛይንና ጥራት መሰረት መጠናቀቃቸውን እንዲሁም መሰረት ልማት የተሟላላቸው መሆኑን ያረጋግጣል ያልተሟሉ ካሉ እነዲሟሉ እንዲሁም የጥራት ችግር ያለባቸው ከተፈጠሩ የማስተካከያ ስራ እንዲከናውን ማድረግ ፤

    4. የተጠናቀቁ ቤቶች ስፋት ፤የተጋሪነት ድርሻ፤ የብሎክን ቤት ቁጥር በዲዛይንና በተፈለገው ሁኔታ መከናውናቸውን በግንባታው ቦታ በመገኝት ማረጋገጥ፤

    5. የተገንቡ ግንባታወች ሙሉና የተደራጀ፤ ዝርዝር የብሎክ እና የቤት መረጃ /book let/ እንዲሁም የተጠናቀቁ ጊዜያዊ ካርታዎችን ማጠናቀቅ እና ማደራጀ፤

    6. የተገንቡ ቤቶችን የማስተላለፊያ ዋጋ ከአጥኚው አካል በመረከብ ማደራጀት፤

    7. የተደራጀ እና የተጠናቀቁ መረጃዎችን ከግንባታ ቅድመ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት በመረከብና በማጣራት ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ማስተላለፍ ዳይሬክቶሬት ያስረክባል፤

    8. በማንኛውም ወቅት በግንባታው ላይ ያሉ መረጃዎችን እና ቤቶች ያሉበትን ደረጃ ለቤት ማስተለላፍ መረጃ መስጠት፤

    9. በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ቤት ማስተላለፍ ከተላለፉ በኃላ ፤ እየተላለፉ ሳለ እና ለተጠቃሚው ተላለፈው ከውስን ጊዜ በኃላ የሚፈጠሩ የጥራት ችግሮች ሲከሰቱና በቤት ማስተላለፍ በኩል ቅሬታ ሲቀርብ መነሻዎቸን በማጠራት መፍትሄ እንዲያገኙ ማድረግ፤

    10. በእጣ የሚተላለፉ ቤቶችን ከተሟላ መረጃ ጋር ለቤቶች ማስተላለፍና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ማስረከብ፤

    11. ግንባታዎች ከተጠናቀቁ በኋላ የመጨረሻ ክፍያ አጠቃላይ ሂደቱ በአግባቡ መከናወኑንና የተሟሉ ሰነዶች መኖራቸውን ያረጋግጣል፣ለስራው የሚከፈሉ ክፍያዎችን ትክክለኛነትም በቅድሚያ ማረጋገጥ፤