21/03/2014

“ቅድሚያ ትኩረት ለህልውና ዘመቻ ļ” በሚል መርህ የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኞች የህልውናው ዘመቻ በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ እያደረጉ ያሉትን ድጋፍ በመቀጠል አጋርነታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዛሬ 21/03/2014 ዓም በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የቅርንጫፍ 10 እና 13 ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሰራተኞች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የቅርንጫፍ 13 ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሰራተኞች በብር 50,160 የሚያወጣ 440 ኪግ ቴምር ድጋፍ ሲያደርጉ፣ የቅርንጫፍ 10 ፐሮጀክት ጽ/ቤት በብር 13,540 ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ ዱቄት እና የተለያዩ አልባሳትን ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን ገልጸዋል፡፡