ጥቅምት 25/2014 ዓ.ም

“ሃገር ስትፈርስ ቆመን አንመለከትም” ከእንግዲህ በአሸባሪው ህውሀትና በኦነግ ሽኔ ለመገዛት የሚፈልግ ልብም ፣ሞራልም የለንም የምንፈልገው መዝመት ነው ሲሉ የአ/አ ቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን ሰራተኞች በውቅታዊ ገዳይ ላይ በየ ዲፓርትመንቱ በተደረገ ውይይት ላይ ጠይቀዋል።

ሃገር ስትፈርስ ቆመን አንመለከትም ሲሉ ሠራተኞቹ አሸባሪው ጁንታ ሃይል ጦርነቱን ህዝባዊ ማድረጉን በአግባቡ በመረዳት ሁሉም ዜጋ ወጥቶ ሃገሩን ለማዳን መዝመት እንዳለበትም ተናግረዋል። የመንግስት ስራን ማሳካት የምንችለው ሀገር ሰላም ስትሆን ነው ፣ቁጭ ብለን ሞት አጠገባችን እስኪመጣ ከመጠበቅ ያሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ ልንዋጋቸው ይገባል ነው ያሉት።

አስተያየት ሰጭዎች አክለውም በከተማችን ብሎም በቤቶች ኮርፓሬሽን ከማእከል እስከ ቅርንጫፍና በጋራ መኖሪያ መንደሮች የተሰገሰጉ የጁንታው ተላላኪዎችን መንጥሮ ለማውጣት ሠራተኛውና ነዋሪዎች ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል ።