እንኳን ወደ የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!
ዳይሬክቶሬቱ አራት ቡድኖች አሉት
- የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ቡድን
- የመንግስት ቤቶች ገቢ ክትትል ቡድን
- የቤቶች ይዞታ ክትትል ቡድን
- የመልሶ ማልማት ቡድን
የዳይሬክቶሬቱ ዓላማ
የዳይሬክቶሬቱን ስራ ስምሪት የመንግስት ቤቶች አስተዳደር መመሪያና ህግ መሠረት አገልግሎት መሰጠቱን፤ የመንግስት ቤቶች ጥራታቸው ተጠብቆ ለህብረተሰቡ ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ የቤት አስተዳደር በከተማው ላይ እንዲኖር በመስራት የህብረተሰቡን ፍላጎት ማርካት፡፡
በዳይሬክቶሬቱና በአራቱ ቡድኖች የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች
- የመንግስት መኖሪያና ንግድ ቤቶችን እንዲሁም በኪራይ የተሰጡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውል እድሳት ክትትል ማድረግ፣
2. በህገወጥ መንገድ የተያዙትንና ሌላ የገዙ፤ በእጣ ኮንደሚኒየም የደረሳቸውና በሌላ በስጦታ፤ በውርስ ያገኙትን ተከራዮች የማስለቀቅ ስራውን መከታተል፣
3. የቤት ችግረኞች፤ የልማት ተነሺዎች ሆነው የመንግስት መኖሪያ ቤት የሚሰጣቸውን መከታተል፣
4. የመንግስት ቤት ይዞታዎች ክትትል ማድረግ፣
5. በመልሶ ማልማት የሚፈለጉ ቦታዎችን መረጃ መረከብ እና የልማት ተነሺዎችን መረጃ ማሰባሰብ፣
6. በልማት የሚነሱ ተነሺዎችን መረጃ መለየት እና ማሰባሰብ እንደ ምርጫቸው ምትክ ቤት እንዲሰጣቸው ወደ ሚመለከተው አካል መላክ፤
7. የመንግስት ቤቶች ኪራይ ገቢን ማሳደግ፤ መግባቱን መከታተል፤
8. የጋራ መኖሪያ ቤት ኪራይ ገቢን ማሳደግ፤ መግባቱን መከታተል፤