እንኳን ወደ ግንባታ ቅድመ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!
ዳይሬክቶሬቱ ሁለት ቡድኖች አሉት
- የመሬት ዝግጅትና ግንባታ ፈቃድ ቡድን
- የዲዛይንና ፕላን ዝግጅት ክትትል ቡድን
በዳይሬክቶሬቱና በሁለቱ ቡድኖች የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች
- ለቤት ግንበታ የሚፈለገውን የለማ መሬት በመጠን ለይቶ እና የሚመለከተውን አካል ጠይቆ ከተሟላ ህጋዊ ሰነዶች ጋር በመረከብ ስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
2. ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ አመታት ለቤት ልማት ሊውሉ የሚችሉ አመች ቦታዎችን በከተማዋ ውስጥ በራሱ በመለየትና በማጥናት ከተሟላ መረጃ ጋር እንዲፈቀድለት ለሚመለከተው አካል ጥያቄ በማቅረብ እና በማስፈቀድ ስራ ላይ ያውላል፣
3. የመሬት አጠቃቀሙ በቁጠባና በጥቂት ቦታ በርካታ ነዋሪዎችን ለማስፈር የሚያስችል
ጥናት በማከናወን ለግንባታው ዲዛይንና የስራ ዝርዝሮች እንዲሰሩ በማድረግ ተገቢውን የጥራት መስፈርት አሟልተው የተሰሩ መሆናቸውን በማረጋገጥ ስራ ላይ ያውላል፣
4. ለቤቶች ግንባታ የሚያስፈልገውን ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላን እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ያዘጋጃል፣
5. ከሚመለከተው አካል የፕላን ስምምነት በማስፈቀድ ተግበራዊ ያደርጋል፣
6. ለኮርፖሬሽኑ የቤት ግንባታ አገልግሎት የሚውለውን መሬት የቶፖግራፊ/ የመልከዓ
ምድርና የግንባታ ሳይቶችን ዙሪያ ገብ የቅየሳ ሥራ ያከናውናል፤ መረጃዎቹን በአግባቡ ይይዛል፤
7. ለቤት ልማት ፕሮግራም የሚውለውን መሬት የአፈር ምርመራ እንዲከናወን በማድረግ፤ መረጃዎችን በአግባቡ ይይዛል፤
8. የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል በማስፈቀድ ስራ ላይ ያውላል፣
9. በየወቅቱ የመሰረተ ልማት አቅርቦቶች ወጪ እንዲቀንሱ የሚያስችሉ ከህንጻዎች ጥግግት አኳያ በጥምረት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚስችሉ ጥናቶችን አዘጋጅቶ ተግበራዊ ያደርጋል፣
10. የህንፃ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከሚመለከተው አካል የመጠቀሚያ ፈቃድ ጠይቆ ስራ ላይ ያውላል፣
11. ግንበታቸው ለተጠናቀቁ ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲዘጋጅ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ በማቅረብና አፀድቆ በመረከብ ስራ ላይ ያውላል፣
12. የዲዛይን ፍላጎት ለሚመለከተው አካል ያቀረባል፤ተፈፃሚነቱን ያስተባብራል፤ይረከባል