ህዳር 13/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች እያደረጉት ያለው ድጋፍ እንደቀጠለ ነው፡፡ የፕሮጀክት 6 ቅ/ጽ/ቤት ሠራተኞችም ከ60 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች በጦርነቱ ለተፈናቀሉ እና ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች 445 ኪሎ ግራም ዱቄት እና የሕፃናት አልሚ ምግብ፣ ከ200 በላይ የአዋቂ እና የሕፃናት አልባሳት እና ጫማዎች እንዲሁም አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ሌሎች የመኝታ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ቀደም ሲልም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እንዲሁም የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች “ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን” በሚል መርህ በሁለት ዙር የደም ልገሳ ሥነ ስርዓት ማካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን በዕለቱ የተደረገው የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እየተካሄደ እንደሆነ እና ቀጣይነት እንደሚኖረውም ለማወቅ ተችሏል፡፡