ህዳር 17/2014 ዓ.ም

የአዲስአበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊታችን እና በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው በመቀጠል ላይ ናቸው፡፡ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የፕሮጀክት 4 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች በየወሩ ከሚቆርጡት ደሞዛቸው እና ከሚለግሱት ደማቸው በተጨማሪ ዛሬ ህዳር 17/2014 ዓም ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል ግምቱ 500 ሺ ብር በላይ የሚሆን የምግብ፣ የአልባሳት እና የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የቅርንጫፍ 4 ጽ/ቤት ሰራተኞች 1250ከ.ግ ዱቄት፣1450 ኪ.ግ ማካሮኒ፣ 110 ካርቶን ፓስታ ፣እያንዳንዳቸው 2000 ሊትር የሚይዙ 2 የውሃ ማጠራቀሚያ ሮቶዎች 60 ካርቶን የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ: እንዲሁም 65 የብርድ ልብስ እና 925 ኪ.ግ ሩዝ ድጋፍ ማድረጋቸውን በርክክብ ፕሮግራሙ ላይ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት በኮርፖሬሽኑ የመዐከል እና የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊታችን እና ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በርክክብ ፕሮግራሙ ላይ ተናግረዋል፡፡