እንኳን ወደ ግዥ ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!
ዳይሬክቶሬቱ ሁለት ቡድኖች አሉት
- የግዥ ቡድን
- የውለታ አስተዳደርና የገበያ ጥናት ቡድን
በዳይሬክቶሬቱና በሁለቱ ቡድኖች የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች
1. በከተማ አስተዳደሩ የግዥ እና የንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 17/2002 እና በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2002 መሰረት በኮርፖሬሽኑ የታቀዱ የስራ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉትን ዕቃዎች እና የአገልግሎት ግዢዎችን በተመጣጣኝ እና በወቅታዊ የገበያ ዋጋ፣ በተፈለገው የጥራት ደረጃ እና በሚፈለገው ጊዜ ወይንም ወቅት በዕቅድ መሰረት ግዥ በመፈፀም ማቅረብ፣ ውለታ ማስተዳደር፣
2. በከተማ አስተዳደሩ የግዥ እና የንብረት ማስወገድ አገልግሎት በኩል የሚገዙ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸው እና በማዕቀፍ የሚገዙ ዕቃዎችን ግዥ መፈፀም፣
3. በግዥ የሚቀርቡ አገልግሎቶች እና ዕቃዎች ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ያላቸው መሆኑን የገበያ ዋጋ ጥናት ማከናወን፡፡