እንኳን ወደ የገበያ ትስስር ስልጠናና ክትትል ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!
ዳይሬክቶሬቱ ሁለት ቡድኖች አሉት
- የስልጠና እና ክትትል ቡድን
- የገበያ ትሥሥር ቡድን
መግቢያ
የገበያ ትስስር ስልጠናና ድጋፍ ክትትል ዳይሬክቶሬት በኮርፖሬሽኑ የሚመደቡ ኢንተርፕራይዞችን የገበያ ትስስር በመፍጠር እና የስልጠና ድጋፍ በማድረግ በቅ/ጽ/ቤቶች ላይ የቤቶች ግንባታ ለኢንተርፕራይዞች ለማጠናከር የሚረዳ ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
በዳይሬክቶሬቱና በሁለቱ ቡድኖች የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች
- በኮርፖሬሽኑ ለኢንተርኘራይዞች የሚፈጠረውን የስራ ዕድል መምራትና መቆጣጠር፣
2. የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የገበያ ትስስርና ሌሎች ሥራዎችን በተመለከተ የተሟላና ወቅታዊ መረጃ መያዛቸውን መከታተልና አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ፣
3. በ18ቱም ቅ/ጽ/ቤቶች የስራ ዕድል የተፈጠረላቸውና በስራ ላይ ያሉ ኢንተርኘራይዞች መረጃ በየጊዜው ወቅታዊ /update/ በማድረግ ማደራጀት፣
4. ለዳይሬክቶሬቱ የተሰጡትን ሥራዎች መከታተያ ቼክሊስት (Checklist) በማዘጋጀት የክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
5. በ18ቱም ቅ/ጽ/ቤቶች የስራ ዕድል የተፈጠረላቸውና በስራ ላይ ያሉ ኢንተርኘራይዞች የስልጠና ፍላጐት በመለየት ስልጠና መስጠት፣
6. በተለየ የአመለካከትና የክህሎት ክፍተት በቅ/ጽ/ቤቶች በገበያ ትስስርና መረጃ ቡድን ውስጥ ላሉ ባለሙያዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠት፣