እንኳን ወደ የቤቶች መረጃ ማኔጅመንትና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!
ዳይሬክቶሬቱ ሁለት ቡድኖች አሉት
- የኔትወርክ ሶፍትዌር ድረ-ገጽ አስተዳደርና ጥገና ቡድን
- የቤት መረጃና ሲስተም ዳታቤዝ አስተዳደር ቡድን
መግቢያ
የቤቶች መረጃ ማኔጅመንትና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የኮርፖሬሽኑን ሰራ በአይሲቲ እንዲደገፍና ወደ ዘመናዊ በቴክኖሎጂ የተደራጀ መረጃ ማኔጅመንት ስርዓት ከመፍጠር ጀምሮ ፍሰቱን በማስተካከል ቀልጣፋና የተቀናጀ አገልግሎት መስጠት ወደ ሚያስችል ደረጃ የማሳደግ አገልግሎት የሚሰጥ ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
የዳይሬክቶሬቱ ዓላማ
ዳታ ሴንተር በማስገንባት የዳታ ቤዝ ስርዓት እንዲኖር ፤ሲስተም እንዲለማ፤የመረጃ ፍሰቱን ለማሳለጥ ተገቢ ሆነ ኢንፍራስትራክቸር እንዲኖር ማድረግ፤ በተቋሙ ውስጥ ዘመናዊ መረጃ ስርዓት እንዲኖር መረጃን በድረገፅ እንዲለቀቅ ድረ-ገፁ እንዲለማ ማድረግ፣ የጥገና አገልግሎት መስጠት እና ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡
በዳይሬክቶሬቱና በሁለቱ ቡድኖች የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች
- የቤቶችን መረጃ ማደራጀት፣
2. ሲስተምና ዳታቤዝ ማስተዳደር፣
3. ለቤት ተመዝጋቢዎች ዕጣ ማውጣት፣
4. የጥገና አገልግሎት መስጠት፣
5. የኔትወርክ ስርዓት መዘርጋት፣
6. ድረ-ገፅ ወቅታዊ ማድረግ፤