ጥቅምት 16/2014 ዓ.ም

በተለያዩ ሳይቶች ግንባታቸው በመፋጠን ላይ ያሉትን የጋራ መኖሪያ በማጠናቀቅ ህብረተሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች የሳይት ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

በቦሌ ቡልቡላ፣ ፉሪ ሃና እና ኮዬ ፈጬ ሳይቶች በተካሄደው የሳይት ጉብኝት ላይ  የቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራር አካላት ከቢሮው እና ከኮርፖሬሽኑ ለተውጣጣው የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ባደረጉት ገለፃ ለፋይናንስ አቅርቦት እንዲሁም ውሃ፣ መብራትና መንገድን ለመሳሰሉ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ትኩረት መስጠት የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ በማጠናቀቅ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ 

የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሪት ያስሚን ወሃብረቢ የፋይናንስ አቅርቦትን እና የመሰረተ ልማት ግንባታን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመሥራት የተቀናጀ አሠራር ለመዘርጋት ጥረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

በሳይት ጉብኝቱ ላይ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እንዲሁም የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች  ተሳታፊ ሆነዋል፡፡