ህዳር 30/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች እያደረጉት ያለው ድጋፍ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ የተለያዩ ቅ/ጽ/ቤት ሠራተኞችም ከ ከ129 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የቅርንጫፍ 3፣ 14፣ 15 እና 18 ጽ/ቤት ሠራተኞች በጦርነቱ ለተፈናቀሉ እና ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች 365 የሴቶች ንጽኅና መጠበቂያ፣ የተለያዩ የአዋቂ እና የሕፃናት አልባሳት ፣38 ኪሎ ግራም መኮረኒ፣ እንዲሁም 30 ካርቶን ፓስታ፣ 5 ኩንታል ሩዝ ፣ ሳሙናዎች፣ 52 ሶፍቶችን እና 4 ካርቶን ዘይት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የቤቶች ማስተላለፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አውራሪስ ከበደ እና የኮርፖሬት ሰርቪስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ አጥናፌ በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ያደረጉት ድጋፍ ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ በመሆኑ የሚበረታታ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

ቀደም ሲልም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እንዲሁም የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች ተመሳሳይ ድጋፍ እና የደም ልገሳ ያደረጉ ሲሆን በዕለቱ የተደረገው የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍም በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አስተባባሪነት ቀጣይነት እንደሚኖረው ለማወቅ ተችሏል፡፡