እንኳን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ድረ-ገጽ በደህና መጡ፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ ህዳር 6/2015 ዓ/ም በይፋ ስነስርዓት አወጣ፡፡

አጠቃላይ 20/80 ነባር ቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር

አጠቃላይ 40/60 ቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር

አጠቃላይ 20/80 አዲስ የቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር

በ20/80 መርሃ ግብር ለእጣ የተዘጋጁ ቤቶች

በ40/60 መርሃ ግብር ለእጣ የተዘጋጁ ቤቶች

በ20/80 መርሃ ግብር ለእጣ ብቁ የሆኑ ተወዳዳሪዎች

በ40/60 መርሃ ግብር ለእጣ ብቁ የሆኑ ተወዳዳሪዎች

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከተማው ነዋሪ የሚሰጠውን አገልግሎት ግልጽ፣ ፈጣንና ውጤታማ እንዲሆንና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በርካታ የለውጥ ስራ ተግባራዊ እያደረገ ሲሆን ከዚህም መካከል የከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት እንደገና በማቋቋም መዋቅራዊ አደረጃጀትና የመሰረታዊ የስራ ሂደት ክለሳ ጥናት በማካሄድ ተቋማት እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡

የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች

የቤት ባለ ቤት የሆኑ

በስራ ላይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች

አመታትን በስራ ላይ

ዜናዎች በከፊል

በኮርፖሬሽኑ የፕሮጀክት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሠራተኞች የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አደረጉ፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች እያደረጉት ያለው ድጋፍ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ የተለያዩ ቅ/ጽ/ቤት ሠራተኞችም ከ ከ129 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የቢሮው የመንግስትና የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና ስልጣንና ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ::

ህብረተሰቡ በየደረጃው የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ለመፍታት የተቀናጀ አሠራር መዘርጋትና በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመንግስትና የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች የ2014 በጀት ዓመት የአራት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም በቢሮው ስልጣንና ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት ከክፍለ ከተማ እና ወረዳ ከተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተካሂዷል፡፡

የፕሮጀክት 4 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች ድጋፋቸውን ቀጥለዋል፡፡

የአዲስአበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊታችን እና በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው በመቀጠል ላይ ናቸው፡፡ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የፕሮጀክት 4 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች በየወሩ ከሚቆርጡት ደሞዛቸው እና ከሚለግሱት ደማቸው በተጨማሪ ዛሬ …

የፕሮጀክት 6 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሠራተኞች የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አደረጉ፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች እያደረጉት ያለው ድጋፍ እንደቀጠለ ነው፡፡ የፕሮጀክት 6 ቅ/ጽ/ቤት ሠራተኞችም ከ60 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች በጦርነቱ ለተፈናቀሉ እና ለችግር ለተጋለጡ

ከ 16 አመታት በላይ በግንባታ ሂደት

የከተማ አስተዳደሩ በካቢኔ ውሳኔ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ለመንግስት ሠራተኞ 5,000 ፣የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተደረገ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ መኖሪያ ቤት የሌላቸውን መምሕራን በልዩ ሁኔታ በማየት የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በኪራይ እንዲሰጣቸው በተወሰነው መሰረት በኪራይ ሲጠቀሙ ቆይተው ከሐምሌ 2013 ዓ.ም አጋማሽ ላይ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ውሳኔ መሰረት ኪራዩ ቀርቶ በስማቸው የሽያጭ ውል ፈፅመው  የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ተወስኗል ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለአንድ ሺ(1,000) የ10/90 ቤቶችን የደሓ ደሓ ነዋሪዎች ከተማ አስተዳደሩ በኪራይ እንዲሰጥ በወሰነው መሰርት ተፈጻሚ ሆኗል ፡፡

ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

ነባር ሆኜ ተመዝግቤ አዲስ ተመዝጋቢ ነህ ተባልኩኝ ለምን?

ስህተቱ የተፈጠረዉ በምዝገባ ወቅት ነበር፣ አሁን ግን በማኔጅመንት  ዉሳኔ መሠረት ወደኋላ ተመልሶ ምዝገባ ማስተካከል እንደማይገባ አቅጣጫ ተሠቷል ስለዚህ  ባሉበት እንዲቆዩ ተደጓል፡፡

40/60 100% ከፍዬ ለምን ቅድምያ አልወጣልኝም?

በከተማ አስተዳደሩ ዉሳኔ መሠረት 40% የቆጠበ ሁሉ እጣ ዉስጥ  እንዲካተት በተወሰነ ዉሳኔ ተቀይሯል::

የባንክ አካውንት ቁጥር ማስተካከል እችላለሁ?

ከባንክ ትክክለኛውን ቁጥር የሚገልጽ በደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅብዎታል፡፡

የስም ስህተት ማስተካከል እችላለሁ?

አሁን ማስተካከል አይችሉም፡፡ ነገር ግን ዕጣ ሲወጣልዎት ከፍርድ ቤት ማስረጃ በማምጣት መስተካከል ይችላል፡፡

እጣ ዉስጥ ለመግባት ምን ያህል መቆጠብ አለብኝ?

ከተመዘገቡ ጀምሮ በየወሩ ሳያቋርጡ ይቆጥቡ፡፡

ለአስተያየትዎ…