በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚከናወኑ ግንባታዎች ተሳታፊ የሚሆኑ ስራ ተቋራጮችን ለመመልመል ለቀረበ የጥሪ ማስታወቂያ ስለማራዘም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚከናወኑ ግንባታዎች ተሳታፊ የሚሆኑ ስራ ተቋራጮችን ለመመልመል ለቀረበ የጥሪ ማስታወቂያ ስለማራዘም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር የመመሪያ ቁጥር 180/2017 ባፀደቀው መሰረት ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 7 የብቃት ማረጋገጫ ያላቸውን የግንባታ ስራ የሚያከናውኑ የስራ ተቋራጮችን ተሳታፊ እዲሆኑ የጥሪ ማስታወቂያ በቀን 14/11/2017ዓ.ም ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ነገር ምልመላውን ለተጨማሪ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ማራዘም በማስፈለጉ ኮርፖሬሽኑ በሚያሰራበት ቁርጥ ዋጋ ለመሳተፍ ፍላጎቱ ያላችሁ በዘርፉ የተሰማራችሁ ስራ ተቋራጮች በድህረ ገፅ www.aahdc.gov.et online ምዝገባ እንድታደርጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ቀርቧል፡-
ሀ) የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
ለ) የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣
ሐ) የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣
መ) የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣
ሠ) የግብር መለያ ቁጥር፣
ረ) ከመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
ሰ) ከገቢዎች ሚኒስቴር ወይም ገቢዎች ቢሮ የተሰጠ በጨረታ መሳተፍ እንደሚችል የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህ መሰረት የሚቀርብ ሆኖ የስራ ተቋራጩ ማህተምና የስራ ተቋራጩ የበላይ ኃላፊ ወይም የህጋዊ ተወካይ ፊርማ ሊያርፍባቸው የሚገባ እና ስራ ተቋራጭ ለምዝገባ የሚሰጠውን ማንኛውንም ሰነድ ለዚያ ወቅትና ተግባር ብቻ እንደሰጠ የሚያሳይ ጽሁፍና ፊርማ ሊያሳርፍበት ይገባል፡፡
ሸ) ምዝገባውንና ውድድሩን አልፎ ስራ ቢሰጠው ማህበራትን እንደሚያሳትፉ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤
ቀ) ምዝገባውንና ውድድሩን አልፎ ስራ ቢሰጠውና ቅድመ ክፍያ ባይከፈለው በራሱ አቅም መስራት እንደሚችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሳተፍ እንደሚቻል ኮርፖሬሽኑ በድጋሚ ያሳውቃል፡-
ማሳሰቢያ፡-
- በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ስር ማህበራት ሆነው ሲሳተፉ የነበሩ ከስራ እና ክህሎት ቢሮ ደረጃ ስለማሻሻላቸው እና ከማህበር ወደ ስራ ተቋራጭነት የዞሩ ስለመሆናቸው የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ ካልቻሉ መወዳደር እንደማይችሉ እናሳስባለን፡፡
- ምዝገባው የሚካሄደው በኦንላይን (Online) ብቻ መሆኑን እያሳወቅን ቢሮ ድረስ በአካል በመምጣት የሚቀርብ ጥያቄን የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን