እንኳን ወደ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!
ዳይሬክቶሬቱ ሁለት ቡድኖች አሉት
- የጋራ መኖሪያ ቤት አስተዳደር ቡድን
- የጋራ መኖርያ ቤቶች ማህበራት ክትትልና ድጋፍ ቡድን
በዳይሬክቶሬቱና በሁለቱ ቡድኖች የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች
ከተላለፉ ቤቶች ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ቅሬታዎች እና የአገልግሎት ጥያቁዎች ምላሽ መስጠት
- የልኬት /ካሬ/ ሜትር ልዩነት ቅሬታ መቀበል
2. የፍሳሽ /ሳኒተሪ/ እና ሌሎች ቅሬታዎችን መቀበል
3. ቅሬታዎቹን መረጃ ማደራጀት
4. የቅሬታዎችን ትክክለኝነት ማረጋገጥ
5. ቅሬታዎቹ እንዲፈቱ ለቴክኒክ ኮሚቴው ማሳወቅ
6. ቅሬታዎቹ መፈታታቸውን ክትትል ማድረግ
7. የአምስት አመት መሙላት ማረጋገጫ ለሚጠይቁ ደንበኞች አገልግሎት መስጠት
ያልተላለፉ ቤቶችን መጠበቅ እና መረጃ ማደራጀት
1. ርክክብ የተፈጸመባቸውን ቤቶች መረጃ መረከብ
2. ግንባታቸው የተጠናቀቁ ቤቶች እጣ አወጥቶ እስኪተላለፉ ድረስ የሚጠበቁበትን ስርአት መዘርጋት፤እየተጠበቁ መሆናቸውን ክትትል ማድረግ
3. ከእጣ በኋላ ያልተላለፉ ቤቶችን በመለየት ማሸግ ከማህበራት ጋር በመነጋገር እንዲጠበቁ ማድረግ
4. የተላለፉ ቤቶችን መረጃ አደራጅቶ መያዝ
5. ከመሬት አስተዳደር በእዳና እገዳ ተመዝግበው ወደ ባንክ የተላኩትን መረጃ አደራጅቶ መያዝ
የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ባለቤቶች ማህበራትን መከታተል መደገፍ
1. የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የሚተዳደሩበት የህግ ማዕቀፎችን በማጥናት የማሻሻያ ግብዓቶች ያቀርባል ወይም አስፈላጊ የአሰራር ሥርቶችን ይዘረጋል፡፡
2. በከተማዋ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበራት የሚተዳደሩበትን የህግ ማዕቀፍ፣ ስልትና ስታንዳርድ ያዘጋጃል፣የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ይሰጣል፡፡
3. የጋራ መኖሪያ ቤት ማህበራት እንዲመሰረቱና በህግ አግባብ ተልእኳቸውን እንዲወጡ ያበረታታል፡፡
4. በጋራ መኖሪያ ቤቶች የማህበራት አደረጃጀት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በማጥናት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ክፍተቶችን የሚሞላ ስርዓት ይዘረጋል፤ ክትትል ያደርጋል፡፡
5. በጋራ መኖሪያ ቤቶች ህብረተሰቡን የሚያውኩ እና ህገ-ወጥ ተግባራትን የሚፈፅሙ አካላትን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ቁጥጥር ያደርጋል፤እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡