እንኳን ወደ የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ገጽ ደህና መጡ!
መግቢያ
የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት በኮርፖሬሽኑ የአደረጃጀት መዋቅር ውስጥ ከተካተቱት ዳይሬክቶሬቶች አንዱ ሲሆን የስትራቴጂክ እና ዓመታዊ ዕቅድ ዝግጅት፣ የበጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ማካሄድ፤ ግብረ-መልስ መስጠት፣ የአፈፃፀም ሪፖርቶች ዝግጅት እና የመሳሰሉት ተግባራትን ለማከነወን የተቋቋመ ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
በዳይሬክቶሬቱ የሚሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች
- የተቋሙን የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ማዘጋጀት፣
2.የተቋሙን የአጭር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ በጀት ማዘጋጀት፣ የበጀት አጠቃቀም ክትትል ማድረግ፣ ግብረ መልስ መስጠት፣
3.የተቋሙን የወር፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ወራትና የዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት፣
4.በዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና አጠቃላይ የግንባታ አፈጻጸም ላይ ለዳይሬክቶሬቶችና ፕ/ቅ/ጽ/ቤቶች ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣
5.የተቋሙን የወር፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ወራትና የዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ፣
6.በዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና አጠቃላይ የግንባታ አፈጻጸም ላይ ለዳይሬክቶሬቶችና ፕ/ቅ/ጽ/ቤቶች ግብረ መልስ መስጠት፤